Ethiopian Shipping and Logistics

Ethiopian Shipping and Logistics Vision
By providing competitive shipping & logistics services, to become a preferred & renowned Afric
(1)

Ethiopian Investment Holdings  (EIH) has officially commenced its 2018 EFY Annual Performance Review Session, beginning ...
24/08/2026

Ethiopian Investment Holdings (EIH) has officially commenced its 2018 EFY Annual Performance Review Session, beginning with Ethiopian Shipping and Logistics (ESL).
During the year, ESL delivered a strong performance, transporting more than 7 million tons of cargo and achieving 28% year-on-year revenue growth. Despite operating primarily along the Red Sea corridor amid heightened security risks and geopolitical disruptions, the company maintained a solid EBITDA margin of 17%, demonstrating business resilience.
As competition in the logistics sector continues to intensify, the review highlighted the need to further strengthen service integration, expand services, and sustain a strong focus on operational efficiency, service quality, and asset utilization. These priorities will be critical to strengthening ESL’s competitive position, enhancing customer value, and supporting sustainable long-term growth.

Source:- EthiopianInvestmentHoldings

የገላን ወደብና ተርሚናል ከቃሊቲ ትራኪንግና ወደብና ተርሚናል ጋር በጋራ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር አከናወኑ፡፡በኢትዮጵያ...
15/08/2026

የገላን ወደብና ተርሚናል ከቃሊቲ ትራኪንግና ወደብና ተርሚናል ጋር በጋራ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር አከናወኑ፡፡

በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የገላን ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ከቃሊቲ ትራኪንግ እና ከቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ጋር በጋራ በመሆን የ2018 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንዲሁም የማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የገላን ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ጉዲሳ ገልጸዋል፡፡
ፕሮግራሙ በገላን ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ቅጽር ግቢ በዛሬው እለት ሲከናወን ፕሮግራሙን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ጉዲሳ ላለፉት ተከታታይ አመታት ከ5,000 በላይ ለምግብነት የሚውሉና እና የአፈር ለምነት እና መሸርሸርን የሚከላከሉ ሃገር በቀል ችግኞች መትከል እንደተቻለ እና ከነዚህም ውስጥ 80 በመቶ በላይ የሚሆኑት በተገቢው ሁኔታ የጸደቁ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በዘንድሮ ዓመት ከሚተከሉት 1,000 ችግኞች መካከል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ለምግብነት የሚሆኑ የችግኝ አይነቶች ሲሆኑ ይህም መንግስት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀል ተግባር እንደሆነ አጽዕኖት በመስጠት አስረድተዋል፡፡
እንደ ስራ አስኪያጁ ገለጻ ከሆነ ችግኞችን መትከል ብቻ ውጤት የሚያመጣ ባለመሆኑ ተከታታይነት ያለው እንክብከቤ በማድረግ የተተከሉ ችግኞች ፍሬ እንዲያፈሩ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ቅ/ጽ/ቤታቸው ለእያንዳዱ የሚተከሉ ችግኞች ባለሙያ በመመደብ ተገቢውን ክትትል እና እንክብካቤ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ይህም ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው የችግኝ ተከላ ስራው ለወጣቶች ተጨማሪ የስራ እድል መፍጠሩንም አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም በእለቱ ከችግኝ ተከላው ፕሮግራም ጎን ለጎን የገላን ወደብና ተርሚናል ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች በራሳቸው ተነሳሽነት መዋጮ በማሰባሰብ በገላን ክፍለ ከተማ ለሚገኙ 64 አቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በእለቱ የደም ልገሳ መርሃ ግብር መከናወኑም ተመላክቷል፡፡
በዕለቱ ከቃሊቲ ትራኪንግ፣ ከቃሊቲ ወደብና ተርሚናል፣ከገላን ወደብና ተርሚናል እና ከገላን ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተውጣጡ አካላት በፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

13/08/2026

Leading the Green Legacy: Planting Hope, Growing the Future.

 #አዲሱን ሳምንት ለመልካም ተነሳሽነት፣ ለላቀ ውጤታማነትና ለዘላቂ ስኬት!ለኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አመራሮችና ሰራተኞች ሳምንቱ የመልካም ተነሳሽነት፣የትጋትና  የውጤታማት ...
10/08/2026

#አዲሱን ሳምንት ለመልካም ተነሳሽነት፣ ለላቀ ውጤታማነትና ለዘላቂ ስኬት!
ለኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አመራሮችና ሰራተኞች ሳምንቱ የመልካም ተነሳሽነት፣የትጋትና የውጤታማት እንዲሆን እንመኛለን፡፡
ለክቡራን ለደንበኞቻችንም ሳምንቱ የስኬትና የፍሬያማነት እንዲሆን ምኞታችን ነው፡፡
አብረን በመሥራት፣ የተሻለ አገልግሎትን በመስጠትና እሴትን በመፍጠር፣ ከባሕር ባሻገር ያለውን ዕድል እንገነባለን!
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ


#መልካም ሳምንት

*ኢባትሎ ዓመታዊ የሠራተኞች ጉባዔውን አካሄደ* የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ (ኢባትሎ) የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸምና የ2019 ዓ.ም ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ ያተኮረ ዓመታዊ ...
08/08/2026

*ኢባትሎ ዓመታዊ የሠራተኞች ጉባዔውን አካሄደ*

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ (ኢባትሎ) የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸምና የ2019 ዓ.ም ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የሠራተኞች ጉባዔ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ቅርንጫፎች አካሄደ።

ዝግጅቱን ከማእከል ሆነው በሁሉም ቅርንጫፎች በብሮድካስት ያስጀመሩት የኢባትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) ፤ ድርጅቱ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ያስመዘገበው የላቀ ውጤት በመላው አመራርና ሠራተኞች ትጋትና ቁርጠኝነት የተገኘ መሆኑን ገልጸው፣ በመጪው አመት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሁሉም የድርጅት ሰራተኞች ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዚህ አመት በልዩ ሁኔታ፤ በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመው ተልዕኳቸውን ሲወጡ ለነበሩት የጊቤ መርከብ ባሕረኞች የዕውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ፣ ጅቡቲ፣ ሞጆ፣ ድሬዳዋ፣ ባሕርዳር፣ ኮምቦልቻ፣ መቀሌ፣ ሰመራና ወረታ በተካሄደው ጉባዔ ወደ 2,500 የሚጠጉ አመራሮችና ሠራተኞች ተሳትፈዋል።

ኢባትሎ እና ኢትዮ ኢንጂነሪንግ የረጅም ጊዜ የሥራ ግንኙነታቸውን ወደ ተሻለ ትብብር ለማሸጋገር ተስማሙ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እና ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከዚህ ቀደም ...
07/08/2026

ኢባትሎ እና ኢትዮ ኢንጂነሪንግ የረጅም ጊዜ የሥራ ግንኙነታቸውን ወደ ተሻለ ትብብር ለማሸጋገር ተስማሙ

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እና ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከዚህ ቀደም በነበራቸው የሥራ ግንኙነት የተነሱ የፋይናንስ ጉዳዮችን በሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት ባለው አግባብ ለመፍታት መግባባት ላይ ደርሰዋል።
በኢባትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ እና በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሸጋው ሙሉጌታ መሪነት በተካሄደው ውይይት፣ ለረጅም ጊዜ ሲካሄድበት የቆየውን ጉዳይ ወደ መፍትሔ ለማምጣት በሚያስችል አሠራር ላይ መግባባት ተችሏል።
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ የኢባትሎ ቁልፍ አጋር እንደሆነ የገለፁት ኢንጅነር አብዱልበር ፤ ይህንንም በሚያሳይ አግባብ በቀጣይነት በልዩ ሁኔታ አብረው የሚሰሩበት አሰራር በቅርቡ እንደሚመቻች ጠቁመዋል።

የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ - ግብር አከናወነ:: በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የባቦጋያ ማሪታይምና ሎ...
06/08/2026

የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ - ግብር አከናወነ::

በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ የ2018 የክረምት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ የመትከል መርሀ - ግብር እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የሚውል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን አቶ ሲራጅ አብዱላሂ የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ ዲን ገለጹ።
እንደ አቶ ሲራጅ ገለጻ በዛሬው ዕለት 500 ሀገር በቀል ችግኞች የተተከሉ ሲሆን አካዳሚው ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በንቃት በመሳተፍ ከችግኝ ተከላ ባለፈ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ፣ የተራቆቱ መሬቶችን በደን በመሸፈን እና የአካባቢ ስነ-ምህዳርን በማጠናከር የሀገሪቱን የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ በተግባር እየደገፈ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ የችግኝ ተከላ መርሀ - ግብር ላይ ከአካዳሚው አመራርና ሠራተኞች በተጨማሪ በወቅቱ ስልጠና ላይ የሚገኙ ሰልጣኞች፣ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሆራ አርሰዲ ወረዳ አመራሮች እና በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል::

ከዚህ በተጨማሪም የአካዳሚው ሠራተኞችና አመራሮች በበጎ ፈቃድ በመሳተፍ ከ71 ሽ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በአካባቢው ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የሚውል 100 ደርዘን ደብተር እና 10 ፓኮ እስክርቢቶ ድጋፍ ተደርጓል::
ይህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በቀጣይም በደም ልገሳ መርሀ-ግብር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል::

04/08/2026

እነሆ ሳምንታዊ ፕሮግራማችን ከዓመቱ የስኬት ጉዞ መግለጫችን ጋር

ኢባትሎ ‹‹ ተስፋን እንትከል›› በሚል መርህ ሀገር የተለመችውን የ800 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ትልም ዕውን ለማድረግ  የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡የኢትዮጵያ የባሕር...
03/08/2026

ኢባትሎ ‹‹ ተስፋን እንትከል›› በሚል መርህ ሀገር የተለመችውን የ800 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ትልም ዕውን ለማድረግ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አመራሮችና ሠራተኞች ‹‹ ተስፋን እንትከል›› በሚል መርህ ሀገር የተለመችውን የ800 ሚሊየን ችግኝ የመትከል ዕቅድ ለማሳካት እንደ ድርጅት 36 ሺህ ችግኞችን በዋና መስሪያ ቤትና በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለመትከል የተያዘው ዕቅድ የመጀመሪያ ዙርና ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም አካል የሆነው የችግኝ መትከል ፕሮግራም የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት ተጀምሯል፡፡
ኢባትሎ በአካባቢው በተለይም በሎሜ ወረዳ በተከታታይ ባከናወናቸው አረንጓዴ አሻራ የማኖር ስራዎች አካባቢያዊ ስነ ምህዳሩን የሚያሰፋና ከባባያዊ የአየር ጥበቃ ላይ የራሱን አሻራ በማሳረፍ ጥብቅ ደን መፍጠር የቻለ ሲሆን ከችግኝ ተከላው ስራ ባሻገር ለአካባቢው ወጣቶችም የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡
የድጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በየዓመቱ በሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ወቅቱን በጉጉት እንደሚጠብቁት ገልፀው በየ ዓመቱ የሚደረገው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በአካባቢው የስነ ምህዳር ለውጥ ላይ እያመጣ ያለውን መልካም ገጽታ በሚመለከቱበት ወቅት ሀሴት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
የኢባትሎ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ፣ የኢባትሎ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎች፣ የዋናው መስሪያ ቤት መካከለኛ አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞችን ጨምሮ በሞጆ ሎስቲክስ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የጉምሩክ አመራችና ሰራተኞች የተሳተፉበት ይኸው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ለዕለቱ የተያዘውን ዕቅድ ማሳካት የተቻለበት ነው፡፡ የተተከሉት ችግኞች ሃገር በቀል ሲሆኑ ለመብል የሚሆኑ ፍራፍሬዎችም የተካተቱበት ነበር፡፡

Maintaining Excellence and Strengthening Reliability: MV Abay II in Dry Dock.  Shipping and Logistics  The Sea!
02/08/2026

Maintaining Excellence and Strengthening Reliability: MV Abay II in Dry Dock.
Shipping and Logistics
The Sea!

Address

Around Leghar
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 12:00

Telephone

+251115518280

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Shipping and Logistics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Shipping and Logistics:

Shortcuts

Share