አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት / ADERA Logistics & Delivery Express /

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት / ADERA Logistics & Delivery Express /

አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት / ADERA Logistics & Delivery Express / Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት / ADERA Logistics & Delivery Express /, Cargo and freight company, Addis Ababa.

እንኳን ወደ አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት በደህና መጡ!

​አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት፣ በየትኛውም የሀገራችን ክልሎች በግለሰብም ሆነ በመስሪያ ቤቶች እንዲሁም በንግድ ድርጅቶች መካከል ለሚደረጉ የሰነድና የዕቃ ልውውጦች ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ጥንቃቄ የተሞላበት አገልግሎት ይሰጣል።

ደንበኞቻችንን በስርዓት እና በትህትና እናገለግላለን።
​የእርስዎ መልዕክት ፣ ለእኛ አደራችን ነው።

የመንገድ እንግልት፣ የጓዝ ጭንቀት እና የትራንስፖርት ውጣ ውረድ አበቃላቸው! አሁን በአንድ ቦታ የሙሉ ጉዞዎን ምቾት የሚያረጋግጡበት ዘመናዊና የተሟላ አገልግሎት አዘጋጅተናል።ሶስቱን አገልግሎ...
29/08/2026

የመንገድ እንግልት፣ የጓዝ ጭንቀት እና የትራንስፖርት ውጣ ውረድ አበቃላቸው! አሁን በአንድ ቦታ የሙሉ ጉዞዎን ምቾት የሚያረጋግጡበት ዘመናዊና የተሟላ አገልግሎት አዘጋጅተናል።

ሶስቱን አገልግሎቶች በአንድ ላይ ሲጠቀሙ የሚገኙ ጥቅሞች፡

1. የጓዝ እና እቃ አስተማማኝ ማጓጓዣ (በአደራ Logistics): ከባድ ጓዝዎንና ዕቃዎን ተሸክመው አይጨነቁ! አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ዕቃዎን ከተነሱበት ቦታ ተረክቦ ባሉበት መዳረሻ በሙሉ ዋስትና ያደርስልዎታል።

2. የበረራ ትኬት አገልግሎት (በበረራ Travel & Tour): ወደሚፈልጉት መዳረሻ የአየር መንገድ ትኬትዎን ያለ ምንም እንግልት፣ በፍጥነት እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንቆርጥልዎታለን።

3. ምቹ የኤርፖርት ታክሲ አገልግሎት: ከቤትዎ ወይም ከቢሮዎ ወደ ኤርፖርት፣ ወይም ከኤርፖርት ወጥተው ወደ መረጡት መዳረሻ በዘመናዊና ምቹ ታክሲዎቻችን በፍጹም ሰላምና ደህንነት እናደርስዎታለን።

“የበረራ ትኬትዎን በ‘በረራ’ ቆርጠው፣ ጓዝዎን በ‘አደራ’ ልከው፣ በታክሲያችን ከተጓዙ በአንድ ድንጋይ ሶስት ወፍ ማለት ይሄ አይደለም?!

ምቾትዎ የደስታችን ምንጭ ነው!”

አድራሻዎቻችን፡
ደብረ ማርቆስ፡ አዲሱ ስታር ህንፃ (ከቴሌ ፊትለፊት፣ ቡና ባንክ ጎን)፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 101 B

አዲስ አበባ፡ አዲሱ ገበያ፣ ከጃንቦ ህንፃ ጀርባ፣ ሸገር ግራንድ ሞል፣ ቢሮ ቁጥር BF- 096

የስልክ ቁጥሮች፡
* 0918 96 96 97
* 0915 36 36 37

አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት እና በረራ የጉዞና ጉብኝት ወኪል — የጉዞዎ አስተማማኝ አጋር!

መልካም ዜና ለክቡራን ደንበኞቻችን! ✈️አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት እህት ኩባንያ የሆነውን "በረራ የጉዞና ጉብኝት" ወኪል  በሚል ስያሜ...
24/08/2026

መልካም ዜና ለክቡራን ደንበኞቻችን! ✈️

አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት እህት ኩባንያ የሆነውን "በረራ የጉዞና ጉብኝት" ወኪል በሚል ስያሜ ማቋቋሙን በደስታ ያበስራል!

ጉዞዎን የበለጠ ምቹ እና ቀልጣፋ የሚያደርጉ አዳዲስ አገልግሎቶችን ይዘንልዎ ቀርበናል፦

✈️ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የአየር መንገድ (የአውሮፕላን) ትኬት መቁረጥ

🚕 ፈጣን፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ የታክሲ አገልግሎት

📅 የፓስፖርት እና የቪዛ ቀጠሮዎችን መያዝ

📞 ይደውሉልን፦ 09-18-96-96-97

📍 አድራሻ፦ ደብረ ማርቆስ ፥ ስታር አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ፣ ከቡና ባንክ ጎን ፥ ቢሮ ቁጥር 102 B

ጉዞዎን በበረራ! ፤ ጓዝዎን በአደራ!

23/03/2026
  ስንመሰርት ታልቅ ህልም እና ግልጽ ራዕይ ስለነበር ፣ በ1 አመት ከ4 ወራት ጉዟችን ከባድና ቀላል ፈተናዎች የገጠሙን ቢሆንም በእግዚአብሔር እርዳታና ለህልማችን ባለን ቁርጠኝነት ምክንያት ...
21/03/2026

ስንመሰርት ታልቅ ህልም እና ግልጽ ራዕይ ስለነበር ፣ በ1 አመት ከ4 ወራት ጉዟችን ከባድና ቀላል ፈተናዎች የገጠሙን ቢሆንም በእግዚአብሔር እርዳታና ለህልማችን ባለን ቁርጠኝነት ምክንያት ዛሬን ለማዬት በቅተናል።

ተቋማችን በአሁኑ ስዓት ወደ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (ኃ.የተ.የግ.ማ/ P.L.C.) አድጎ በስኬት ጎዳና ላይ ይገኛል። 🚀

🔵 ምን አዲስ ነገር አለ?

🔶የቅርንጫፎቻችንን ቁጥር በቅርቡ በመጨመር ወደ እርስዎ ይበልጥ እንቀርባለን!

🔶ዘመናዊና ፈጣን አሰራሮችን በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን!

🔶ዓለም አቀፍ ተቋም የመሆን ራዕያችንን ለማሳካት በትጋት እየሰራን እንገኛለን!

🔵 እናንተ ለደንበኞቻችን፦

ምግብና መጠጦችን ጨምሮ ማንኛውንም መልክቶቻችሁን አምናችሁ አደራ ላላችሁን ድርጅቶችና ግለሰቦች በሙሉ፣ በእኛ መተማመናችሁ ለስኬታችን መሰረት ሆኖናል። እናመሰግናለን! 🙏ነገም ከትናንቱ በላቀ ትጋት እናገለግላችኋለን!

🔵 ከመነሻችን ጀምሮ በሐሳብና በተግባር አብራችሁን ለነበራችሁ ወንድም አህቶቻችን ፣ የስራ ባልደረቦቻችን እና ጓደኞቻችን ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው።

🔵 በአደራ ቢሮ ቤተሰብነት አብራችሁን ለዘለቃችሁም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ለተለያችሁን የአደራ በሙሉ ለአደራ ዛሬ ላይ መድረስ አሻራችሁ አለበትና ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።

አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ💡

ታማኝነት፣ ፍጥነት፣ ጥራት!

ማስታወቂያ !አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ / Adera Logistics & DeliveryExpress Service PLC.ማንኛውንም አይነት መልዕክት ከደብረ ማርቆስ - አዲ...
09/03/2026

ማስታወቂያ !

አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ / Adera Logistics & Delivery
Express Service PLC.

ማንኛውንም አይነት መልዕክት ከደብረ ማርቆስ - አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ - ደብረ ማርቆስ በፍፁም ታማኝነትና ኃላፊነት የማድረስ አገልግሎት መስጠት ከጀመርን እነሆ አንድ ሙሉ አመት ተሻገርን።

የደንበኞቻችንን ፍላጎት የሚመጥን ሰፊ፣ ምቹ እና አስተማማኝ የስራ ቦታ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የደብረ ማርቆስ ቅርንጫፋችንን ቀድሞ ከነበርንበት "የኛ ህንፃ" ወደ "ስታር አዲሱ ህንፃ የገበያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101B ከቡና ባንክ ጎን" ማዛወራችንን እንገልፃለን። በመሆኑም ከየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ደንበኞቻችን ወደ አዲሱ የስራ ቦታችን በመምጣት አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እናበስራለን።

ድርጅታችን አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ በሌሎችም ከተማዎች ቅርንጫፎቹን ለመክፈት እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

ስለምንሰጣቸው አዳዲስ አገልግሎቶቻችን በቀጣይ በዝርዝር የምናስተዋውቅ ይሆናል!!

አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር / Adera Logistics & Delivery Service PLC.

ADERA Logistics & Delivery Express P.L.C. 🤞
23/11/2025

ADERA Logistics & Delivery Express P.L.C.

🤞

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አደራ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት / ADERA Logistics & Delivery Express / posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share